ቀን ፡-03/13/2012 ዓ.ም
ጋምቢ ህክምና እና ቢዝነስ ኮሌጅ ለ2013 ዓ.ም የት/ት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ እና በሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን በኦንላይን ምዝገባ የጀመረ መሆኑን እያሳወቅን መመዝገብ የሚፈልግ ሁሉ በኮሌጁ ድረገጽ ማለትም https://gambyteachinghospital.com/college ላይ በተቀመጠዉ ኦንላይን መመዝገቢያ ፕላት ፎረም በመግባት ማመልከት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጡ ፕሮግራሞች
በጤናው ዘርፍ በመደበኛ ፕሮግራም የሚሰጡ
- በህክምና ዶክትሬት
- በህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ
- በክሊኒካል ፋርማሲ
- በሚድዋይፈሪ
- በነርስነትና
- በህክምና ላቦራቶሪ እንዲሁም
በቢዝነስ የትምህርት መስክ ደግሞ በመደበኛዉና በተከታታይ መርሀ ግብር
- በማኔጅመንት
- በአካውንቲንግና ፋይናንስ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የመግቢያ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
በሁለተኛ ዲግሪ የሚሰጡ ፕሮግራሞች ደግሞ
- ማስተርስ በቢዝነስ አስተዳደር(MBA)
- አካዉንቲግና ፋይናንስ
- ማስተርስ በህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ(MPH)
የመግቢያ መስፈርት (ለህከምና ዶክትሬት)
- በ2011 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው (በእንግሊዝኛ፣በሂሳብ፣ በአፕቲቲዩድ እና በፊዚክስ) 200 እና በላይ
- በ2010 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 450 እና በላይ
- በ2009 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 450 እና በላይ
- በ2008 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 470 እና በላይ
- በ2007 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 450 እና በላይ
- ከ2007 ዓ.ም በፊት የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 400 እና በላይ
- ከ500 የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተፈትነው 300 እና በላይ ያስመዘገቡ
ለማመልከቻ የሚያስፈልጉ
- የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
- የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት
- የማመልከቻ ክፍያ 500 ብር መክፈል እና ደረሰኝ ማያያዝ
የመግቢያ መስፈርት( ለሌሎች ሙያዎች)
- በ2011 ዓ.ም ፣ ለተፈጥሮ ሳይንስ (በእንግሊዝኛ፣በሂሳብ፣ በአፕቲቲዩድ እና በፊዚክስ) እንዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ (በእንግሊዝኛ፣ በሂሳብ፣ በአፕቲቲዩድ እና በጅኦግራፊ) ተደምረው 140 እና ከዚያ በላይ ከዚያ በላይ
- 2010 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 295 እና በላይ
- በ2009 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 295 እና በላይ
- በ2008 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 295 እና በላይ
- በ2007 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 275 እና በላይ
- በ2006 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 250 እና በላይ
- በ2005 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 265 እና በላይ
- በ2003 ዓ.ም እና ከዚያ በፊት የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና የወሰዱ ከሆነ ደግሞ የዩኒቨርሲት መግቢያ ያላቸዉ፡፡
- ለማመልከቻ የሚያስፈልጉ
በ12ኛ ክፍል የሚያመለክቱ
- የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
- የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት
- የማመልከቻ ክፍያ 300 ብር መክፈል እና ደረሰኝ ማያያዝ
በዲፕሎማቸው ለሚያመለክቱ ደግሞ
- በጤና ሙያ ዲፕሎማ / ደረጃ 4 ያጠናቀቀ/ች
- የደረጃ 4 የብቃት ምዘና (የሌብል ቤዝድ) ማስረጃ ያለው/ላት
- አንድ ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ላት
- ኮሌጁ የሚሰጠዉን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል
- የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት
- ከ9-10ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
- የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት
- ኦፊሻል ከምዝገባ በፊት ቀድሞ ማስላክ የሚችል
- የማመልከቻ ክፍያ 300 ብር መክፈል እና ደረሰኝ ማያያዝ
- የማመልከቻ ጊዜ
✍️ ከጳጉሜ 4 /2012 – መስከረም 20/2013 ዓ.ም
ማሳሰቢያ፡-
- ማንኛዉም አመልካች የራሱ የሆነ ኢሜል(E Mail) አድራሻ ሊኖረዉ ይገባል፡፡
- ፕላት ፎረሙ ላይ የተቀመጡ ነገሮችን በሙሉ አንብቦ በትክክል መሙላት ይኖርበታል፡፡
- አንድ አመልካች አንዴ ብቻ ነዉ መሙላት የሚጠበቅበት፡፡
- በአካል መጦ መመዝገብ አይቻልም፡፡
- አብሮ የተያያዘውን የዉል ስምምነት እና ማመልከቻ ፎርሙን በማውረድ (Download) በማድረግ በመሙላት scan አድርጋችሁ ማያያዝ ይኖርባችኋል፡፡
- የትምህርት ማስረጃችሁን በአንድ PDF ፋይል ፎርማት ብቻ scan አድርጋችሁ ማያያዝ ይኖርባችኋል (Maximum 2 MByte)
የድርጅቱ የሂሳብ ቁጥር፡ 1000158098777
Click here for Application