ጋምቢ ህክምና እና ቢዝነስ ኮሌጅ ለ2013 ዓ.ም የት/ት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ምዝገባ የጀመረ መሆኑን እያሳወቅን ምዝገባ የሚከናወንባቸዉ የት/ት መስኮች እንደሚከተለዉ ተቀምጠዋል፡፡
በመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጡ ፕሮግራሞች
- በጤናው ዘርፍ በመደበኛ ፕሮግራም የሚሰጡ
- በህክምና ዶክትሬት (Medicine)
- በህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ
- በሚድዋይፈሪ
- በነርስነትና
- በህክምና ላቦራቶሪ ሳይንስ እንዲሁም
- በቢዝነስ የትምህርት መስክ ደግሞ
- በማኔጅመንት
- በአካውንቲንግና ፋይናንስ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የመግቢያ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
- የመግቢያ መስፈርት ለህከምና ዶክትሬት (Medicine)
-
- በ2012/13 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 450 እና በላይ
- በ2011 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው (በእንግሊዝኛ፣በሂሳብ፣ በአፕቲቲዩድ እና በፊዚክስ) 200 እና በላይ
- በ2010 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 450 እና በላይ
- በ2009 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 450 እና በላይ
- በ2008 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 470 እና በላይ
- በ2007 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 450 እና በላይ
- ከ2007 ዓ.ም በፊት የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 400 እና በላይ
- ከ500 የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተፈትነው 300 እና በላይ ያስመዘገቡ
ለማመልከቻ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች
- የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዋናዉ 1 ኮፒ ጋር
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናዉ 1 ኮፒ ጋር
- የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ዋናዉ 1 ኮፒ ጋር
- 3 ፎቶ ግራፍ
- የማመልከቻ ክፍያ 550 ብር መክፈል እና የአንድ ወር ወርሀዊ ክፍያ
የመግቢያ መስፈርት( ለሌሎች ሙያዎች)
- 2012/13 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው
- ወንድ 330 እና በላይ
- ሴት 320 እና በላይ
- ታዳጊ ክልል ተማሪ (በሁሉም ፆታ) 310 እና በላይ
- በ2011 ዓ.ም ፣ ለተፈጥሮ ሳይንስ (በእንግሊዝኛ፣በሂሳብ፣ በአፕቲቲዩድ እና በፊዚክስ) እንዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ (በእንግሊዝኛ፣ በሂሳብ፣ በአፕቲቲዩድ እና በጅኦግራፊ) ተደምረው 140 እና ከዚያ በላይ ከዚያ በላይ
- 2010 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 295 እና በላይ
- በ2009 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 295 እና በላይ
- በ2008 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 295 እና በላይ
- በ2007 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 275 እና በላይ
- በ2006 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 250 እና በላይ
- በ2005 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 265 እና በላይ
- በ2004 ዓ.ም የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው 265 እና በላይ
- በ2003 ዓ.ም እና ከዚያ በፊት የአገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና የወሰዱ ከሆነ ደግሞ የዩኒቨርሲት መግቢያ ያላቸዉ፡፡
ለማመልከቻ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች
በ12ኛ ክፍል የሚያመለክቱ
- የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዋናዉ 1 ኮፒ ጋር
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናዉ 1 ኮፒ ጋር
- የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ዋናዉ 1 ኮፒ ጋር
- 3 ፎቶ ግራፍ
- የማመልከቻ ክፍያ 300 ብር መክፈል እና የአንድ ወር ወርሀዊ ክፍያ
በዲፕሎማቸው ለሚያመለክቱ ደግሞ
- በጤና ሙያ ዲፕሎማ / ደረጃ 4 ያጠናቀቀ/ች
- የደረጃ 4 የብቃት ምዘና (የሌብል ቤዝድ) ማስረጃ ያለው/ላት
- አንድ ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ላት
- ኮሌጁ የሚሰጠዉን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል
- የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት
- ከ9-10ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
- የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት
- ኦፊሻል ከምዝገባ በፊት ቀድሞ ማስላክ የሚችል
- 3 ፎቶ ግራፍ
- የማመልከቻ ክፍያ 300 ብር መክፈል እና የአንድ ወር ወርሀዊ ክፍያ
የማመልከቻ ጊዜ
✍️ ከሚያዚያ 4/2013 – ሚያዚያ 9/2013 ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ ፡ ሬጅስትራር ቢሮ (ቢሮ ቁጥር 206)